mirage

አማርኛ እንደ አፍ መፍቻ ቋንቋ በሚል ተሻሽሎ በቀረቡት የአምስተኛ እና የስድስተኛ ክፍል መማሪያ መጻህፍት ውስጥ የተካተቱ የቃላት ትምህርት ይዘቶች አደረጃጀትና አቀራረብ ግምገማ

DSpace Repository

Show simple item record

dc.contributor.author መንግስቱ, ንጉሴ
dc.date.accessioned 2021-12-03T11:33:12Z
dc.date.available 2021-12-03T11:33:12Z
dc.date.issued 2021-09-24
dc.identifier.uri http://hdl.handle.net/123456789/4577
dc.description.abstract የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ የመጀመሪያ ደረጃ ሁለተኛ እርከን የአማርኛ እንደ አፍ መፍቻ ቋንቋ በሚል ተሻሽሎ በቀረቡት የ5ኛ እና የ6ኛ ክፍል የአማርኛ መማሪያ መጻህፍት ውስጥ የቃላት ትምህርት ይዘት አደረጃጀትና አቀራረብ በመመርመር የትምህርቱን ጠንካራና ደካማ ጎን በመለየት እንዲሁም ደካማ ጎኖቹ ስለሚጠናከሩበት መንገድ አስተያየት መሰንዘር ነው፡፡ የጥናቱን ዓላማ ከግብ ለማድረስ የሚያስችሉ መረጃዎችን ለማግኘት የሰነድ ፍተሻ ተግባራዊ ተደርጓል፡፡ ሰነድ ፍተሻ የተተኳሪውን መጽሀፍ የቃላት ትምህርት አደረጃጀትና አቀራረብ መረጃ ለመሰብሰብ አግዟል፡፡ የተሰበሰበው መረጃ በአይነታዊ ወይም በገላጭ የትንተና ዘዴ በሰንጠረዥ በመታገዝ በቁጥር፣በመቶኛና በቃላት አማካኝነት ተተንትነዋል፡፡ የተገኘው ውጤትም በሁሉም መጽሀፍ ውስጥ የቃላት ትምህርት ተገቢ ትኩረት እንዳገኙ፤የቃላት ትምህርት ይዘቶች ተገቢ ትኩረት እንደተሰጣቸውና ወጥነት ባለው መልኩ ከመጽሀፍ መጀመሪያ እስከ መጨረሻ እንደቀረቡ፤የቃላት ፍች ከአውዳቸው ለመገመት እንደቻሉና መልመጃዎች ታስበውበት እንደተዘጋጁ፤የቃላት ትምህርት አደረጃጀታቸው ተከታታይነት፣ተለጣጣቂነትና ውህድነት ባለው መልኩ እንደተደራጁ ጥናቱ ጠቁሟል፡፡የቃላት ፍች፣የቃላት አጠቃቀምና አገባብ እንዲሁም የቃላት ምስረታና እርባታ ትኩረት እንደተሰጠው ተስተውሏል፡፡ የከታች ተከታች የፍች ዝምድና ብዙም ትኩረት እንዳልተሰጠው ተጠቁሟል፡፡ በሁሉም የክፍል ደረጃ ለቃላት ፍካሬያዊና ዘይቤያዊ ፍች ተገቢ ትኩረት እንዳልተሰጠው፤እንዲሁም ፈሊጣዊ ንግግር ከ5ኛ ክፍል ውጪ ተገቢ ትኩረት አልተሰጠውም፡፡ ትምህርቱ በቀጥተኛና በኢቀጥተኛ አቀራረብ ከማንበብ፣ከመጻፍ፣ከማዳመጥና ከሰዋስው ትምህርት ጋር ተቀናጅቶ እንደቀረበ፤መጽሀፍ አውዳዊ ፍች ተመሳስሎና ተቃርኖ፣የቢጋር ሰንጠረዥ፣ማዛመድ፣የምዕላድ ትንተና በገላፃ ወይም በማብራሪያ ስልቶች በጥቅም ላይ እንደዋሉ፤የመዝገበ ቃላት አጠቃቀም ጥበብን እንዲካኑ የሚያግዝ ትምህርት በ6ኛ ክፍል በመጠኑም ቢሆን ለማሳየት ሲሞክርም በ5ኛ ክፍል መጽሀፍ ውስጥ ግን ሊታይ አለመቻሉ ተስተውሏል፡፡ በመጨረሻም ጥናቱ የመማሪያ መጽሀፍ የቃላት ትምህርት ይዘት አደረጃጀትና አቀራረብ ችግሮችን ለመቅረፍ ያስችላሉ ያሏቸውን የሚጠቁሙ አስተያየቶች ተሰንዝረዋል፡ en_US
dc.description.sponsorship uog en_US
dc.language.iso en_US en_US
dc.publisher uog en_US
dc.subject አደረጃጀትና አቀራረብ ችግሮችን ለመቅረፍ ያስችላሉ ያሏቸውን የሚጠቁሙ አስተያየቶች ተሰንዝረዋል፡ en_US
dc.title አማርኛ እንደ አፍ መፍቻ ቋንቋ በሚል ተሻሽሎ በቀረቡት የአምስተኛ እና የስድስተኛ ክፍል መማሪያ መጻህፍት ውስጥ የተካተቱ የቃላት ትምህርት ይዘቶች አደረጃጀትና አቀራረብ ግምገማ en_US
dc.type Thesis en_US


Files in this item

This item appears in the following Collection(s)

Show simple item record

Search in the Repository


Advanced Search

Browse

My Account