Abstract:
የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ የመጀመሪያ ደረጃ ሁለተኛ እርከን የአማርኛ እንደ አፍ መፍቻ ቋንቋ በሚል ተሻሽሎ
በቀረቡት የ5ኛ እና የ6ኛ ክፍል የአማርኛ መማሪያ መጻህፍት ውስጥ የቃላት ትምህርት ይዘት አደረጃጀትና
አቀራረብ በመመርመር የትምህርቱን ጠንካራና ደካማ ጎን በመለየት እንዲሁም ደካማ ጎኖቹ
ስለሚጠናከሩበት መንገድ አስተያየት መሰንዘር ነው፡፡ የጥናቱን ዓላማ ከግብ ለማድረስ የሚያስችሉ
መረጃዎችን ለማግኘት የሰነድ ፍተሻ ተግባራዊ ተደርጓል፡፡ ሰነድ ፍተሻ የተተኳሪውን መጽሀፍ የቃላት
ትምህርት አደረጃጀትና አቀራረብ መረጃ ለመሰብሰብ አግዟል፡፡ የተሰበሰበው መረጃ በአይነታዊ ወይም
በገላጭ የትንተና ዘዴ በሰንጠረዥ በመታገዝ በቁጥር፣በመቶኛና በቃላት አማካኝነት ተተንትነዋል፡፡
የተገኘው ውጤትም በሁሉም መጽሀፍ ውስጥ የቃላት ትምህርት ተገቢ ትኩረት እንዳገኙ፤የቃላት
ትምህርት ይዘቶች ተገቢ ትኩረት እንደተሰጣቸውና ወጥነት ባለው መልኩ ከመጽሀፍ መጀመሪያ እስከ
መጨረሻ እንደቀረቡ፤የቃላት ፍች ከአውዳቸው ለመገመት እንደቻሉና መልመጃዎች ታስበውበት
እንደተዘጋጁ፤የቃላት ትምህርት አደረጃጀታቸው ተከታታይነት፣ተለጣጣቂነትና ውህድነት ባለው መልኩ
እንደተደራጁ ጥናቱ ጠቁሟል፡፡የቃላት ፍች፣የቃላት አጠቃቀምና አገባብ እንዲሁም የቃላት ምስረታና
እርባታ ትኩረት እንደተሰጠው ተስተውሏል፡፡ የከታች ተከታች የፍች ዝምድና ብዙም ትኩረት
እንዳልተሰጠው ተጠቁሟል፡፡ በሁሉም የክፍል ደረጃ ለቃላት ፍካሬያዊና ዘይቤያዊ ፍች ተገቢ ትኩረት
እንዳልተሰጠው፤እንዲሁም ፈሊጣዊ ንግግር ከ5ኛ ክፍል ውጪ ተገቢ ትኩረት አልተሰጠውም፡፡ ትምህርቱ
በቀጥተኛና በኢቀጥተኛ አቀራረብ ከማንበብ፣ከመጻፍ፣ከማዳመጥና ከሰዋስው ትምህርት ጋር ተቀናጅቶ
እንደቀረበ፤መጽሀፍ አውዳዊ ፍች ተመሳስሎና ተቃርኖ፣የቢጋር ሰንጠረዥ፣ማዛመድ፣የምዕላድ ትንተና
በገላፃ ወይም በማብራሪያ ስልቶች በጥቅም ላይ እንደዋሉ፤የመዝገበ ቃላት አጠቃቀም ጥበብን እንዲካኑ
የሚያግዝ ትምህርት በ6ኛ ክፍል በመጠኑም ቢሆን ለማሳየት ሲሞክርም በ5ኛ ክፍል መጽሀፍ ውስጥ ግን
ሊታይ አለመቻሉ ተስተውሏል፡፡ በመጨረሻም ጥናቱ የመማሪያ መጽሀፍ የቃላት ትምህርት ይዘት
አደረጃጀትና አቀራረብ ችግሮችን ለመቅረፍ ያስችላሉ ያሏቸውን የሚጠቁሙ አስተያየቶች ተሰንዝረዋል፡