mirage

‹‹አእምሯዊ የመማር ብልሃቶችን በግልፅ ማስተማር አንብቦ የመረዳት ችሎታን በማጎልበት ረገድ ያለው አስተዋጽኦበአምባጊዮርጊስ አንደኛ ደረጃና ሙሉ ሳይክል ትምህርት ቤት በ7ኛ ክፍል ተተኳሪነት፡፡››

DSpace Repository

Show simple item record

dc.contributor.author ፈጠነ, ባንቻምላክ
dc.date.accessioned 2021-02-23T08:27:01Z
dc.date.available 2021-02-23T08:27:01Z
dc.date.issued 2013-09-05
dc.identifier.uri http://hdl.handle.net/123456789/3322
dc.description.abstract የዚህ ጥናት ዋና አላማ በአዕምሯዊ ማንበብን የመማር ብልሃት አንብቦ የመረዳት ችሎታን በማጎልበት ረገድ ለተማሪዎች በግልፅ በማስተማር ያለውን ሚና ለመመርመር ነው፡፡የጥናቱ ተሳታፊዎች በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤትየሚገኙ የ2012 ዓ.ም የ7ኛ ክፍል ተማሪዎች የነበሩ 60 ወንድ እና 60 ሴት በድምሩ 120 ተማሪዎች ሲሆኑ ጥናቱ መሰረት ያደረገውም ከፊል ሙከራዊ ዘዴ ናሙና ተመርጦ ተወስዷል፡፡ከጥናቱ ተሳታፊዎችም በፅሑፍ መጠይቅ እና በፈተና መረጃዎች ተሰብስበዋል፡፡የተሰበሰቡትም መረጃዎች በT-test በSPSS soft ware መረጃ መተንተኛ ተሰልተው ትንታኔ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ቅድሚያ በአዕምሯዊ ብልሃት ቀድመው ተምረው ስለነበር ስለ ርዕሰ ጉዳዩ ምን ያህል ተገንዝበዋል የሚለውን ለማወቅ በድህረ-ትምህረት ጥያቄዎች ተሰጥተዋል፡፡ድህረትምህርት ፈተናውም በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ማለትም አዕምሯዊ ብልሃቶችን መማር አንብቦ ለመረዳት ያለውን ጠቀሜታ ከማሳየት አንፃር በቅድመ ልምምድ የሙከራ ቡድን የአንብቦ መረዳት ውጤት በአማካይ = 33.7 መደበኛ ልይይት = 0.48 ነው፡፡በቅድመ ልምምድ የቁጥጥር ቡድኑ የአንብቦ መረዳት ውጤት ደግሞ አማካይ 33.8ሲሆን በነፃ ናሙና ቲ-ቴስት የተገኘው ደግሞ=1.6 ሲሆን የ ፒ ዋጋ p>0.05 ነው፡፡ ይህም የሚያሳየው በቅድመ ልምምዱ በሁለቱም ቡደኖች መካከል ልዩነታቸዉ የጎላ አለመሆኑን ነው፡፡በድህረ ልምምዱ የሙከራ ቡድን የአንብቦ መረዳት ውጤትን ስንመለከት አማካይ = 40.4 ሲሆን መደበኛ ልይይቱ = 10.01 ነው፡፡ በድህረ ልምምዱ የቁጥጥር ቡድን የአንብቦ መረዳት ውጤት አማካይ = 34.4 ነው፡፡መደበኛ ልይይቱ = 7.1 ነዉ፡፡ በነፃ ናሙና ቲ-ቴስት ሲሰላ =40.4 ሆኗል፡፡በሁለቱ ቡድን መካከል የተገኘው የፒ ዋጋ p< 0.05 ሲሆን ይህም የሚያሳየዉ የፅሑፍ መረጃ ስታቲካዊ ስሌትም ከድህረ -ትምህርት ፈተናው ጋር ሲታይ (በ6) ነጥብ መብለጥን ያሳየ ሲሆን፡፡ይኸውም አዕምሯዊ ብልሃቶችን መማር አንብቦ ለመረዳት ያለውን ጠቀሜታ አሳይቷል፡፡ በዚህ ጥናታዊ ፅሑፍ መነሻ ሃሳብ በመውሰድ ወደፊት ቢደረጉ መልካም ናቸው የተባሉትን ሃሳቦች ለማቅረብ ያህል ይህ ጥናታዊ ፅሑፍ የማንበብ ብልሃቶችን አቀናጅቶ ማስተማር የተሻለ ለውጥ እንደሚያመጣ የተገለጸበት ሁኔታ ስለአለ የጥናቱ ትኩረት የነበረው ብልሃቶችን በግልፅ ለተማሪዎች ማሰልጠን የሚል ስለሆነ ዕቅድ ተይዞ በቋሚነት በባለሙያ የተደገፈ ስልጠና ለመምህራን ቢሰጥ፡፡ ሌላው በዚህ ጥናት የተተገበሩትን ሳይሆን አጥኚዎች የምርምር ሂደቱን ቀይረው ማለትም አንብቦ የመረዳት ችግር ያጋጠማቸውን ተማሪዎች ተዛምዷዊ በሆነ መንገድ ለማጥናት ቢሞከር፡፡ en_US
dc.description.sponsorship uog en_US
dc.language.iso other en_US
dc.publisher uog en_US
dc.relation.ispartofseries report;
dc.subject በመጨረሻም በዚህ ጥናታዊ ፅሑፍ ውስጥ የጥናቱ ተተኳሪ ተማሪዎች በአንብቦ መረዳትና በብልሃት አጠቃቀማቸው መሰረት በማድረግ መርምሮ ግኝቱን አንፀባርቋል በመሆኑም ለወደፊት ደግሞ ብልሃቶችን ከአንብቦ መረዳት ጋር በማያያዝ ፆጻን መሰረት በማድረግ ቢጠና፡፡ en_US
dc.title ‹‹አእምሯዊ የመማር ብልሃቶችን በግልፅ ማስተማር አንብቦ የመረዳት ችሎታን በማጎልበት ረገድ ያለው አስተዋጽኦበአምባጊዮርጊስ አንደኛ ደረጃና ሙሉ ሳይክል ትምህርት ቤት በ7ኛ ክፍል ተተኳሪነት፡፡›› en_US
dc.type Thesis en_US


Files in this item

This item appears in the following Collection(s)

Show simple item record

Search in the Repository


Advanced Search

Browse

My Account