Abstract:
የዚህ ጥናት ዋና አላማ በአዕምሯዊ ማንበብን የመማር ብልሃት አንብቦ የመረዳት ችሎታን
በማጎልበት ረገድ ለተማሪዎች በግልፅ በማስተማር ያለውን ሚና ለመመርመር ነው፡፡የጥናቱ
ተሳታፊዎች በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤትየሚገኙ የ2012 ዓ.ም የ7ኛ ክፍል ተማሪዎች የነበሩ 60
ወንድ እና 60 ሴት በድምሩ 120 ተማሪዎች ሲሆኑ ጥናቱ መሰረት ያደረገውም ከፊል ሙከራዊ
ዘዴ ናሙና ተመርጦ ተወስዷል፡፡ከጥናቱ ተሳታፊዎችም በፅሑፍ መጠይቅ እና በፈተና መረጃዎች
ተሰብስበዋል፡፡የተሰበሰቡትም መረጃዎች በT-test በSPSS soft ware መረጃ መተንተኛ ተሰልተው
ትንታኔ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ቅድሚያ በአዕምሯዊ ብልሃት ቀድመው ተምረው ስለነበር ስለ ርዕሰ ጉዳዩ
ምን ያህል ተገንዝበዋል የሚለውን ለማወቅ በድህረ-ትምህረት ጥያቄዎች ተሰጥተዋል፡፡ድህረትምህርት
ፈተናውም
በዚህ
ርዕሰ
ጉዳይ
ማለትም
አዕምሯዊ
ብልሃቶችን
መማር
አንብቦ
ለመረዳት
ያለውን
ጠቀሜታ
ከማሳየት አንፃር በቅድመ ልምምድ የሙከራ ቡድን የአንብቦ መረዳት ውጤት
በአማካይ = 33.7 መደበኛ ልይይት = 0.48 ነው፡፡በቅድመ ልምምድ የቁጥጥር ቡድኑ የአንብቦ
መረዳት ውጤት ደግሞ አማካይ 33.8ሲሆን በነፃ ናሙና ቲ-ቴስት የተገኘው ደግሞ=1.6 ሲሆን የ
ፒ ዋጋ p>0.05 ነው፡፡ ይህም የሚያሳየው በቅድመ ልምምዱ በሁለቱም ቡደኖች መካከል
ልዩነታቸዉ የጎላ አለመሆኑን ነው፡፡በድህረ ልምምዱ የሙከራ ቡድን የአንብቦ መረዳት ውጤትን
ስንመለከት አማካይ = 40.4 ሲሆን መደበኛ ልይይቱ = 10.01 ነው፡፡ በድህረ ልምምዱ የቁጥጥር
ቡድን የአንብቦ መረዳት ውጤት አማካይ = 34.4 ነው፡፡መደበኛ ልይይቱ = 7.1 ነዉ፡፡ በነፃ ናሙና
ቲ-ቴስት ሲሰላ =40.4 ሆኗል፡፡በሁለቱ ቡድን መካከል የተገኘው የፒ ዋጋ p< 0.05 ሲሆን ይህም
የሚያሳየዉ የፅሑፍ መረጃ ስታቲካዊ ስሌትም ከድህረ -ትምህርት ፈተናው ጋር ሲታይ (በ6)
ነጥብ መብለጥን ያሳየ ሲሆን፡፡ይኸውም አዕምሯዊ ብልሃቶችን መማር አንብቦ ለመረዳት ያለውን
ጠቀሜታ አሳይቷል፡፡
በዚህ ጥናታዊ ፅሑፍ መነሻ ሃሳብ በመውሰድ ወደፊት ቢደረጉ መልካም ናቸው የተባሉትን ሃሳቦች
ለማቅረብ ያህል ይህ ጥናታዊ ፅሑፍ የማንበብ ብልሃቶችን አቀናጅቶ ማስተማር የተሻለ ለውጥ
እንደሚያመጣ የተገለጸበት ሁኔታ ስለአለ የጥናቱ ትኩረት የነበረው ብልሃቶችን በግልፅ ለተማሪዎች
ማሰልጠን የሚል ስለሆነ ዕቅድ ተይዞ በቋሚነት በባለሙያ የተደገፈ ስልጠና ለመምህራን ቢሰጥ፡፡
ሌላው በዚህ ጥናት የተተገበሩትን ሳይሆን አጥኚዎች የምርምር ሂደቱን ቀይረው ማለትም አንብቦ
የመረዳት ችግር ያጋጠማቸውን ተማሪዎች ተዛምዷዊ በሆነ መንገድ ለማጥናት ቢሞከር፡፡