Abstract:
የዚህ ጥናት ዋና አላማ በ11ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መጻሕፍት ውስጥ የተካተቱት የማዳመጥ
ክሂል ትምህርት ይዘቶች አደረጃጀት፣ አቀራረብና የክፍል ውስጥ አተገባበር መገምገም ነው፡፡
በመሆኑም ጥናቱ ገላጭ ንድፍን መሰረት ያደረገ ነው፡፡ ይህንን ጥናት ከዳር ለማድረስ አስፈላጊ
የሆኑ መረጃዎች የተገኙት ከሰነድ ፍተሻ፣ ከመምህራን ቃለ መጠይቅና ከክፍል ውስጥ ምልከታ
ነው፡፡ በመሆኑም በምርምር ጥያቄ ቁጥር አንድ ላይ በ11ኛ ክፍል በተዘጋጀው የአማርኛ ቋንቋ
መጻሕፍት ውስጥ የቀረቡ የማዳመጥ ይዘቶች አደረጃጀት ምን ይመስላል የሚለውን የምርምር
ጥያቄ ለመመለስ ግልጋሎት ላይ የዋሉት መረጃ መሰብሰቢያዎች ሰነድ ፍተሻና ቃለ መጠይቅ
ሲሆኑ የተሰበሰቡት መረጃዎች በቁጥር የማይገለጹ በመሆናቸው በአይነታዊ የምርምር ዘዴ በትረካ
መልክ ተተንትነዋል፡፡ በዝግ የምልከታ መከታትያ ቅጽ የተሰበሰበው መረጃ ደግሞ በቁጥርና
በመቶኛ ተሰልቶ መጠናዊ የምርምር ዘዴን በመጠቀም ተተንትኖ ቀርቧል፡፡ የምርምር ጥያቄ
ሁለት የዚህ ጥናት ዋና አላማ በ11ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መጻሕፍት ውስጥ የተካተቱት
የማዳመጥ ክሂል ትምህርት ይዘቶች አቀራረብ ምን ይመስላል የሚለውን የምርምር ጥያቄ
ለመመለስ ግልጋሎት ላይ የዋሉት ሰነድ ፍተሻና ቃለ መጠይቅ ሲሆኑ የተሰበሰቡት መረጃዎች
በቁጥር የማይገለጹ በመሆናቸው በአይነታዊ የምርምር ዘዴ በትረካ መልክ ተተንትነዋል፡፡ በዝግ
የምልከታ መከታትያ ቅጽ የተሰበሰበው መረጃ ደግሞ በቁጥርና በመቶኛ ተሰልቶ መጠናዊ
የምርምር ዘዴን በመጠቀም ተተንትኖ ቀርቧል፡፡ የመጨረሻው የምርምር ጥያቄ የዚህ ጥናት ዋና
አላማ በ11ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መጻሕፍት ውስጥ የተካተቱት የማዳመጥ ክሂል ትምህርት
ይዘቶች የክፍል ውስጥ አተገባበር ምን ይመስላል? የሚለውን የምርምር ጥያቄ ለመመለስ
ግልጋሎት ላይ የዋለው መረጃ መሰብሰቢያ ምልከታ ሲሆን ከምልከታ የተገኘውን መረጃ በቁጥርና
በመቶኛ ተሰልቶ መጠናዊ የምርምር ዘዴን በመጠቀም ተተንትኗል፡፡ከመረጃ መሰብሳቢዎች
በተገኘው ግኝት መሰረት ከይዘት አደረጃጀት አንጻር ከቀላል ወደ ከባድ ይዘቶች አለመደራጀ፣
ከሌሎች የትምህርት አይነቶች ጋር ጎናዊ ዝምድና ያለመኖር፤ ከይዘት አቀራረብ አንጻር ንዑሳን
የማዳመጥ ክሂሎችን በሙሉ አካቶ የመቅረብ ክፍተት መኖር፣በቂ የልምምድ እድል የሚሰጡ
ይዘቶችን ያለማቅረብ፣ የማዳመጥ ክሂል መሳሪያዎችን በስፋት በመማሪያ መጽሐፉ ያለመካተት
ችግሮች እንዳሉ ከሰነድ ፍተሻና ከመምህራን ቃለ መጠይቅ የተገኘው መረጃ አረጋግጧል፡፡
ከክፍል ውስጥ አተገባበር አንጻር ደግሞ መምህራን ምንም አይነት መርጃ መሳሪያ
አለመጠቀማቸውን የምልከታ ጥናቱ አመልክቷል፡፡ በመጨረሻም ጥናቱ አሉ ላላቸው ችግሮች
ማጠቃልያና የመፍትሄሀሳቦች ተሰንዝረዋል፡