mirage

አማርኛ እንደአፍ መፍቻ ቋንቋ በተዘጋጁ የ6ኛ፣ የ7ኛ እና 8ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መጽሃፍት ውስጥ የተካተቱ ሥነጽሑፋዊ ይዘቶች አመራረጥ እና አደረጃጀት ፍተሻ

DSpace Repository

Show simple item record

dc.contributor.author አድጎ, ፈንታየ
dc.date.accessioned 2022-03-01T06:11:05Z
dc.date.available 2022-03-01T06:11:05Z
dc.date.issued 2013-01-18
dc.identifier.uri http://hdl.handle.net/123456789/4653
dc.description.abstract የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ የስድስተኛ፣ የሰባተኛና ስምንተኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መጽሃፍት ውስጥ የተካተቱትን ስነጽሁፋዊ ይዘቶች አመራረጥና አደረጃጃት መፈተሽ ነው፡፡ በጥናቱም እነዚህን ክፍሎች በዓላማ ተኮር ናሙና በመምረጥ በሰነድ ፍተሻ አማካኝነት መረጃው ተሰብስቧል፡፡ የመረጃ መሰብሰቢያ መስፈርቶችም በአብዛኛው የላዛር(1993)እና ሂል (1986) መስፈርቶችን በመጠቀም የተከናወነ ሲሆን ዓይነታዊ የመረጃ አተናተንን በመጠቀም መረጃው ተተንትኗል፡፡ በትንተናው መሰረት የተገኘው የጥናቱ ውጤት እንደሚያሳየውም በነዚህ ተተኳሪ መፃህፍት ውስጥ የስነፅሁፍ ስራዎች አመራረጥና አደረጃጀትን በተመለከተ አብዛኛዎቹ በመርሁ ወይም በተቀመጡት መስፈርት መሰረት የተመረጡ ሆነው ተገኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በሶስቱም የክፍል ደረጃዎች መመሪያ መጽሀፍ ውሰጥ የተካተቱ ስነጽሁፋዊ ስራዎች ከክፍል ክፍል የተለያየ መጠን ያላቸዉ ናቸው፡፡ ማለትም ሰባተኛ ክፍል ስድስት፣ ና ስምንተኛ ክፍል ሰባት ስድስተኛ ክፍል ስምንት ሲሆኑ ሰባተኛናስምንተኛ የተካተቱት በቁጥር አነስተኛ መሆናቸውን ጥናቱ አሳይቷል ፡፡ በመጨረሻም የተመረጡት ስነፅሀፋዊ ስራዎች ስልታዊ በሆነ መንገድ በትምህርቱ መጀመሪያ የቀረበ ይዘት ሳይቋረጥ አስከ ትምህርቱ መጨረሻ ስፋትና ጥልቀት በሚያሳይ ሁኔታ ስነፅሁፋዊ ስራዎች ከሚሰጡት ፋይዳ አንፃር ፣ ከቀላል ወደ ከባድ፣ ተከታታይነትና ተለጣጣቂነት የማቅረቡ ተግባር በአመዛኙ በመስፈርቱ መሰረት በስድስተኛ ክፍል መማሪያ መጽሀፍ ትኩረት ያገኘ ሲሆን በሁለቱ ክፍሎች (ሰባተኛና ስምንተኛ) ክፍል መማሪያ መፃህፍቶች ግን ትኩረት ያላገኙ መሆኑ በጥናቱ ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡ በስነፅሁፋዊ ስራዎች መሳሪያነት ቋንቋን የማስተማር ተግባር በተለይ በዝቅተኛ የክፍል ደረጃ ላይ ለሚማሩ ተማሪዎች ስለሚኖራቸው ሚና ልዩ ትኩረት በመስጠት በመማሪያ መፃህፍቱ ውስጥ የሚካተቱት ስነጽሁፋዊ ይዘቶች ተገቢ በሆነ መልኩ መመረጥ እንዳለባቸውና ሲመረጡ አብዛኛዎቹ የቋንቋ ባለሙያዎች የተስማሙባቸውን የአመራረጥና አደረጃጀት መርሆዎችን ተከትለው እንዲተገብሩ ጥረትማድረግ እንደሚገባ የመፍትሄ ሀሳቦችን ይህ ጥናት ጠቁሟል፡፡ en_US
dc.description.sponsorship uog en_US
dc.language.iso other en_US
dc.publisher uog en_US
dc.relation.ispartofseries Report;
dc.subject የስድስተኛ፣ የሰባተኛና ስምንተኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መጽሃፍት ውስጥ የተካተቱትን ስነጽሁፋዊ ይዘቶች አመራረጥና አደረጃጃት መፈተሽ ነው፡፡ en_US
dc.title አማርኛ እንደአፍ መፍቻ ቋንቋ በተዘጋጁ የ6ኛ፣ የ7ኛ እና 8ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መጽሃፍት ውስጥ የተካተቱ ሥነጽሑፋዊ ይዘቶች አመራረጥ እና አደረጃጀት ፍተሻ en_US
dc.type Thesis en_US


Files in this item

This item appears in the following Collection(s)

Show simple item record

Search in the Repository


Advanced Search

Browse

My Account