Abstract:
የዚህ ጥናት ዋነኛ ዓላማ የመጻፍ ብልሃቶች የተማሪዎችን ድርሰት የመጻፍ ችሎታ እና የመጻፍ ግለ
ብቃትን ለማሻሻል ያለው አስተዋጽኦን መመርመር ነው፡፡ የጥናቱ ተሳታፊዎች በሰሜን ጎንደር
በዳባት ወረዳ አጠቃላይ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2013 ዓ.ም ሰባተኛ ክፍል ደረጃ
ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ ከሚገኙት 600 ተማሪዎች መካከል በእድል ሰጭ ናሙና
ዘዴ የተመረጡ የ7ኛሠ ክፍል 57 ተማሪዎች ናቸው፡፡ በፈተና፣በፅሁፍ መጠይቅ አስፈላጊ
የሆኑ መረጃዎች ተሰብስበዋል ጥናቱም በአንድ ቡድን ላይ ብቻ የሚያተኩር በመሆኑ የአንድ
ክፍል ተማሪዎች በሙሉ በጥናቱ ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ የተማሪዎችን ቁጥር በዚህ መወሰን
ያስፈለገው ጥናቱ በቅድመ ፍትነታዊ ላይ የተመሰረተ በመሆኑ ነው፡፡ የተሰበሰቡት መረጃዎች
በጥናት ናሙና ቲ-ቴስት ተሰልተው በገላጭና በድምዳሚያዊ ስታስቲክስ ተተንትነዋል፡፡
በውጤት ትንተናው መሠረት በቅድመ ትምህርትና በድህረ ትምህርት ፈተና አማካይ ውጤት
መካከል በስታስቲክስ ጉልህ ልዩነት (P<0.05) ታይቷል፡፡ ይህም የመጻፍ ብልሃቶች
የተማሪዎችን የመጻፍ ችሎታ እና የመጻፍ ግለ ብቃት እንደሚያሻሽል(የጥናቱ ውጤት
አመላክቷል፡፡ ከዚህም በመነሳት በጥናቱ መጨረሻ ምዕራፍ ላይ ድምዳሜ እና እሰተያየቶች
እንዲቀርቡ ተደርጓል፡፡