mirage

በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት የቃላት መማር ብልሃት አጠቃቀም ፣ የቋንቋ መማር ስልት ምርጫ እና የቃላት እውቀት ተዛምዶ ጾታ ተኮር ጥናት፤ (በዘጠነኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት)

DSpace Repository

Show simple item record

dc.contributor.author ተሾመ, በአስማረች
dc.date.accessioned 2021-12-03T11:55:56Z
dc.date.available 2021-12-03T11:55:56Z
dc.date.issued 2021-02-21
dc.identifier.uri http://hdl.handle.net/123456789/4581
dc.description.abstract የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት የቃላት መማር ብልሃት አጠቃቀም ፣ የቋንቋ መማር ስልት ምርጫ እና የቃላት እውቀት ተዛምዶ ከጾታ አንጻር መፈተሽ ነው፡፡ ጥናቱ ተዛምዷዊ ንድፍን ተከትሏል፡፡ የጥናቱ ተሳታፊዎች በመተማ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት በ2012 ዓ.ም በዘጠነኛ ክፍል ተመዝግበው በመከታተል ላይ የነበሩ 134 ተማሪዎች ናቸው፡፡ የተማሪዎችን የቃላት መማር ብልሃት አጠቃቀምን እና የቋንቋ መማር ስልት ምርጫን ለመፈተሽ የጽሑፍ መጠይቅ ተግባር ላይ ሲውል፣ የተማሪዎችን የቃላት እውቀት ለመፈተሽ ፈተና በመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያነት አገልግሏል፡፡ ትንተናውም የቃላት መማር ብልሃት አጠቃቀምና የቃላት እውቀት እንዲሁም የቋንቋ መማር ስልት ምርጫና የቃላት እውቀት ተዛምዶ ከጾታ አንጻር በፒርሰን የተዛምዶ መወሰኛ ቀመር ተሰልቷል፡፡ የቃላት መማር ብልሃት አጠቃቀምና የቋንቋ መማር ስልት ምርጫ የቃላት እወቀትን መተንበይ - አለመተንበያቸውን ደግሞ በህብረ ድህረት ትንተና ተሰልቷል፡፡ በትንተናውም በቃላት መማር ብልሃት አጠቃቀምና በቃላት እውቀት መካከል ከጾታ አንጻር በወንዶችም ሆነ በሴቶች ተዛምዶ አለመኖሩን አመላክቷል፡፡ ውጤቱም በወንዶች (r=.013፣ P=.915) በሴቶች ደግሞ (r=.004፣ P=.983) ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ የቃላት መማር ብልሃት የተማሪዎችን የቃላት እውቀት የመተንበይ ድርሻ ደግሞ በሴቶችም ሆነ በወንዶች በጣም ዝቅተኛ ነው፡፡ በቋንቋ መማር ስልት ምርጫ እና በቃላት እውቀት መካከል በወንዶች የተሻለ በሴቶች ደግሞ ዝቅተኛ የተዛምዶ ደረጃ እንዳለው አሳይቷል፡፡ ውጤቱም በወንዶች(r=.376፣p=0.002)፤ በሴቶች ደግሞ (r=102፣p .415) እንደሆነ ታይቷል፡፡ የቋንቋ መማር ስልት ምርጫ የቃላት እውቀትን የመተንበይ ድርሻ የማየት የቋንቋ መማር ስልት ምርጫ በወንዶች የቃላት እውቀትን በመተንበይ ከፍተኛውን ቦታ ሲይዝ፣ የማዳመጥ የቋንቋ መማር ስልት ምርጫ ደግሞ በሴቶች የቃላት እውቀትን በመተንበይ ድርሻ በሁለተኛ ደረጃ ተቀምጧል፡፡ ከቃላት መማር ብልሃት እና ከቋንቋ መማር ስልት ምርጫ ከጾታ አንጻር የቃላት እውቀትን የበለጠ መተንበይ የሚችለው የቋንቋ መማር ስልት ምርጫ እንደሆነ ጥናቱ አመላክቷል፡፡ ውጤቱም የቃላት መማር ብልሃት ለወንዶች የቃላት እውቀት (B = -.005 ፣ t= -.042 ፣ p>0.05) ፤ ለሴቶች ደግሞ (B =.052 t= 382, p>0.05) በሆነ ውጤት አስተዋጾ እንደሌለው አመላክቷል፡፡ በአንጻሩ የቋንቋ መማር ስልት ምርጫ ለወንዶች የቃላት እውቀት (B =.376 t=3.272, p<.005) በሆነ ውጤት አስተዋጾው የጎላ መሆኑን ሲያመላክት ለሴቶች ደግሞ (B =.123 t=.900, p>0.05) በሆነ ውጤት የጎላ ባይሆንም አስተዋጾ እንዳለው ያመለክታል፡፡ ስለሆነም ከግኝቱ በመነሳት የቃላት መማር ብልሃት ከቃላት እውቀት ጋር በወንዶችም ሆነ በሴቶች የዝምድና ደረጃው በጣም ዝቅተኛ ነው፤ የመማር ስልት ምርጫ ከቃላት አውቀት ጋር በወንዶች የተሻለ የዝምድና ደረጃ አሳይቷል፤ እንዲሁም የቋንቋ መማር ስልት ምርጫ ከቃላት መማር ብልሃት አጠቃቀም በተሻለ የቃላት እወቀትን የመተንበይ ድርሻ አለው ብሎ መደምደም ይቻላል፡፡ በአጠቃላይ በተማሪዎች የቃላት መማር ብልሃት አጠቃቀም እና በቃላት እውቀት መካከል በወንዶችም ሆነ በሴቶች ተዛምዶ እንዳልታየ ፤ በተማሪዎች የቋንቋ መማር ስልት ምርጫ እና በቃላት እውቀት መካከል ደግሞ የተዛምዶ ደረጃ መኖሩን ማወቁ በአማርኛ ቋንቋ በተለይም በቃላት ትምህርት ለመማሪያ መጽሐፍ አዘጋጆችና ለመምህራን የተማሪዎችን የቃላት መማር ብልሃት አጠቃቀም በማሻሻልና የቋንቋ መማር ስልት ምርጫን በማጎልበት የቃላት ችሎታቸውን ለማሳደግ በሚደረገው ጥረት የመማር ማስተማር ስነ ዘዴዎችን ለመፈተሽ እንዲሁም ውጤታማ አተገባበርን ለመቃኘት ያግዛል፡፡ en_US
dc.language.iso en_US en_US
dc.publisher uog en_US
dc.subject ለማሳደግ በሚደረገው ጥረት የመማር ማስተማር ስነ ዘዴዎችን ለመፈተሽ እንዲሁም ውጤታማ አተገባበርን ለመቃኘት ያግዛል፡፡ en_US
dc.title በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት የቃላት መማር ብልሃት አጠቃቀም ፣ የቋንቋ መማር ስልት ምርጫ እና የቃላት እውቀት ተዛምዶ ጾታ ተኮር ጥናት፤ (በዘጠነኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት) en_US
dc.type Thesis en_US


Files in this item

This item appears in the following Collection(s)

Show simple item record

Search in the Repository


Advanced Search

Browse

My Account