mirage

የአንብቦ መረዳት ችሎታና የማንበብ ተነሳሽነት ንፅፅር፤ፆታ ተኮር ጥናት

DSpace Repository

Show simple item record

dc.contributor.author አንዳርጌ, ፍትፍቴ
dc.date.accessioned 2021-02-23T07:53:38Z
dc.date.available 2021-02-23T07:53:38Z
dc.date.issued 2013-09-12
dc.identifier.uri http://hdl.handle.net/123456789/3313
dc.description.abstract የዚህ ጥናት ዋና አላማ በ10ኛ ክፍል ሴትና ወንድ ተማሪዎች መካከል የአንብቦ መረዳት ችሎታና የማንበብ የተነሳሽነት ልዩነት መኖሩን ወይም አለመኖሩን መፈተሽ ነው፡፡ ተሳታፊዎች በመካነኢየሱስ ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት በ2012ዓ.ም ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ የሚገኙ በዕጣ ንሞና የተመረጡ 100 የአስረኛ ክፍል (48 ወንድና 52 ሴት) ተማሪዎች ናቸው፡፡ ከተሳታፊዎች መረጃ የተሰበሰበው በሁለት የተለያዩ የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴዎች ነው፡፡ እነሱም የጽሁፍ መጠይቅና ፈተና ናቸው፡፡ ፈተናው አንብቦ መረዳት ችሎታን፤ መጠይቁ የማንበብ ተነሳሽነትን የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴ በመሆን አገልግለዋል፡፡ የተሰበሰቡት መረጃዎች አስተማማኝነትና ተገቢነት ተሰልቶ ከተረጋገጠ በኋላ ሁሉም መረጃዎች በገላጭ ስታትስቲክሶች አማካኝነት ተተንትነው ተብራርተዋል፡፡ የተገኘው መረጃ የፓራሜትሪያዊ መፈተሻ ዘዴዎችን ለመጠቀም የሚያስችል በመሆኑ ተግባራዊ የተደረጉት የመተንተኛ ዘዴዎች አማካይ ውጤት/mean/፣ ልይይት/variance/፣ መደበኛ ልይይት/standard deviation/ ትንተና እና የነጻ ናሙና ቲ-ቴስት ናቸው፡፡ የተማሪዎች የአንብቦ መረዳት ችሎታ መካከለኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ እና የማንበብ ተነሳሽነታቸው ደግሞ 92.6/120X100=77.22% መሆኑን ጥናቱ አሳይቷል፡፡ በጥናቱ ትንተና መሰረት የታየው የአንብቦ መረዳት ችሎታ እና የማንበብ ተነሳሽነት በፆታ ልዩነት እንዳለው መቃኘት ሲሆን የሴቶች አማካይ የአንብቦ መረዳት ችሎታና የማንበብ ተነሳሽነት ከወንዶች የተሻለ ሆኖ ቢገኝም በሁለቱ መካከል ያለው ልዩነት ጉልህ እንዳልሆነ በትንተናው ተረጋግጧል፡፡ የአስረኛ ክፍል ከ120 የወንድ ተማሪዎች የማንበብ ተነሳሽነት አማካይ ውጤት 90.96 ሲሆን የሴት ተማሪዎች የማንበብ ተነሳሽነት 94.23 ሆኗል፤ከ20 የወንዶች የአንብቦ መረዳት ችሎታ 17.02 ፤ የሴቶች የአንብቦ መረዳት ችሎታ 17.87 ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ከዚህ ውጤት በመነሳትም የመፍትሄ ሀሳቦች ተሰጥተዋል፡፡ en_US
dc.description.sponsorship uog en_US
dc.language.iso other en_US
dc.publisher uog en_US
dc.relation.ispartofseries report;
dc.subject ፈተናው አንብቦ መረዳት ችሎታን፤ መጠይቁ የማንበብ ተነሳሽነትን የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴ በመሆን አገልግለዋል፡፡ en_US
dc.title የአንብቦ መረዳት ችሎታና የማንበብ ተነሳሽነት ንፅፅር፤ፆታ ተኮር ጥናት en_US
dc.type Thesis en_US


Files in this item

This item appears in the following Collection(s)

Show simple item record

Search in the Repository


Advanced Search

Browse

My Account