mirage

በመምህራን የሚሰጡ አስተካካይ ምጋቤ ምላሾች የተማሪዎችን ድርሰት የመፃፍ ችሎታ በማሻሻል ረገድ ያላቸው ሚና፤ በ11ኛ ክፍል ተተኳሪነት

DSpace Repository

Show simple item record

dc.contributor.author ጌታሁን, ፈንታነሽ
dc.date.accessioned 2021-02-23T06:33:34Z
dc.date.available 2021-02-23T06:33:34Z
dc.date.issued 2013-09-22
dc.identifier.uri http://hdl.handle.net/123456789/3292
dc.description.abstract የዚህ ጥናት ዓቢይ አላማ በጯሂት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመምህራን የሚሰጡ አስተካካይ ምጋቤ ምላሾች የተማሪዎችን ድርሰት የመጻፍ ችሎታ በማሻሻል ረገድ ያላቸውን ሚና በአስራ አንደኛ ክፍል ተተኳሪነት መመርመር የሚል ሲሆን በዚህ ስር የተካተቱት ንዑሳን ዓላማዎች ደግሞ በመምህራን የሚሰጥ አስተካካይ ምጋቤ ምላሽ ድርሰት የመጻፍ ችሎታን የሚያሳድጉ መሆን አለመሆናቸውን መመርመርና ተማሪዎች በመምህራን በሚሰጣቸው ምጋቤምላሽ ዙረያ ያላቸው አጠቃላይ አስተያየት መፈተሽ፤የሚሉት ናቸው፡፡ ይህን ዓላማ ለማሳካት ጥናቱ መጠናዊ ምርምር የተከተለ ነው፡፡ ባለ ሁለት ቡድን ከፊል ፍትነታዊ የምርምር ንድፍን የተከተለ ነው፡፡ የጥናቱ ተሳታፊ ተማሪዎችም በጯሂት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከሚማሩ ተማሪዎች መካከል ለጥናቱ የተመረጡት የአስራ አንደኛ ክፍል ተማሪዎችን ነው፡፡ ከሌሎቹ የክፍል ደረጃዎች ይልቅ 11ኛ ክፍል በዓላማ ተኮር ናሙና የተመረጠ ሲሆን የክፍሉ ተማሪዎች በአካታች ናሙና በጥናቱ ተሳትፈዋል፡፡ እነዚህ ተማሪዎች በሙከራና በቁጥጥር ቡድን በመክፈል በሙከራ ቡድን ሃያ አንድ ተማሪዎች አስተካካይ የፅሁፍ ምጋቤ ምለሽ በመስጠትና ለቀሪዎቹ ሃያ አንድ ተማሪዎች ደግሞ በቁጥጥር ቡድን ምንም ዓይነት አስተካካይ የፅሁፍ ምጋቤ ምለሽ ባለመስጠት ለለአምሰት ሳምንት በቀን ለሁለት ሰዓት ድርሰት በመፃፍ እንዲለማመዱ ተደርጓል፡፡ ለጥናቱ መረጃ የተሰበሰበበት መሳሪያ የቅድመና የድህረ የድርሰት ልምምድ ፈተናዎች ናቸው፡፡ በፈተና የተገኙት መረጃዎች በጥንድ ናሙና ቲ-ቴስት (Paired Samples t-test) የስሌት ቀመር አማካኝነት ተሰልተው የተገኘውን ውጤት ተተንትኖ ቀርቧል፡፡ በመረጃ ትንተናው መሰረት በሙከራና በቁጥጥር ቡድኖች በቅድመና በድህረ ፈተና ውጤት መካከል የጎላ ልዩነት ተገኝቷል P<0.001 ፡፡ አስተካካይ ምጋቤ ምላሽ የተሰጣቸው ተማሪዎች ከሌላው ቡድን ይልቅ በጉልህ ደረጃ ከፍተኛ አማካይ ውጤት አስመዝግበዋል፡፡ በተመሳሳይ በእያንዱ ቡድን የቅድመና የድህረ ልምምድ ፈተና ውጤት መካከል የአማካይ ውጤት ልዩነት ጉልህ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ በመሆኑም በአስተካካይ የፅሁፍ ምጋቤ ምላሽ መስጫ ዘዴዎች ምጋቤ ምላሽ የተሰጣቸው ተማሪዎች ድርሰት የመፃች ችሎታ መሻሻል አሳይቷል፡፡ በመሆኑም የአማርኛ ቋንቋ መምህራን አስተካካይ ምጋቤ ምላሽ በመጠቀም ድርሰት መፃፍን ቢያስተምሩ የተማሪዎች ድርሰት የመፃፍ ችሎታ ይሻሻላል፡፡ en_US
dc.description.sponsorship uog en_US
dc.language.iso other en_US
dc.publisher uog en_US
dc.relation.ispartofseries report;
dc.subject በመሆኑም የአማርኛ ቋንቋ መምህራን አስተካካይ ምጋቤ ምላሽ በመጠቀም ድርሰት መፃፍን ቢያስተምሩ የተማሪዎች ድርሰት የመፃፍ ችሎታ ይሻሻላል፡፡ en_US
dc.title በመምህራን የሚሰጡ አስተካካይ ምጋቤ ምላሾች የተማሪዎችን ድርሰት የመፃፍ ችሎታ በማሻሻል ረገድ ያላቸው ሚና፤ በ11ኛ ክፍል ተተኳሪነት en_US
dc.type Thesis en_US


Files in this item

This item appears in the following Collection(s)

Show simple item record

Search in the Repository


Advanced Search

Browse

My Account